ወያነ “ራሱ ሰውን ገድሎ ልቅሶ ይደርሳል! ራሲ ገርፎ ራሱ ይጮዃል” እንደተባለው ራሱ በፈጠረው ችግር አዛኝ መስሎ
ለመታየት በወገኖቻችን ላይ የተፈጠረው ችግር በስተጀርባ ከሱዕዲ መንግስት ጋር በመመሳጠር በዜጎች ላይ በመዝመት
ሁኔታውን እያወሳሰበ ይገኛል። ወያነ እውነት ለህዝቡ ክብርና ጥብቅና ቢኖረው ኖሮ የተፈጠረውን ችግር ለዓለም
ማሕበረሰብና ለሳውዲ መንግስት ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝብ ድርጊቱን በመንግስት ደረጃ ማውገዝና ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ
መውሰድ ይችል ነበር። ነገር ግን አላደረገም። ለምን?
1) ወያነ ከአፈጣጠሩም ሆነ ባህርዩ ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና ብሄራዊ ጥቅም ጋር የሚቃረን ስለሆነ የባዕድ አገልጋይና
መሳሪያ ከመሆን አልፎ የህዝብ ጠበቃ መሆን አይችልም። አብዛኞቹ በስልጣን ላይ ያሉት የወያነ ባለስልጣኖች በሳውዲና
በሌሎች ዓረብ ሀገሮች የገንዝብና የማተሪያል ድጋፍ አዲስ አበባ የገቡ ናቸው። ስለዚ ሳውዲ ለወያነ ባለውለታው እንጂ
ጠላቱ አይደለም።
2) የሳውዲ መንግስት በኢትዮጵያ የነገስታቱ ሸሪክ በመሆን የወያነ መንግስትና የኢኮኖሚ አውታሮች የሚቆጣጠሩ እንደነ
ሸክ አላሙዲንን የመሳሰሉት የሳውዲ ቱጃሮች ወኪሎች አሉዋቸው። በአሁኑ ጊዜ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሳውዲ ዶላርና
የሸኩ ገንዘብ ያልቀመሰ የወያነ/ኢሕአዴግ ባለስልጣን አለ ቢባል ውሸት ነው። ስለዚህ በፔትሮ ዶላር የተሸበበ የባለስልጣን
አፍ ደፍሮ የሳውዲ መንግስትን ያወግዛል ብሎ ማሰብ የማይሆን ነው።
3) የወያነ ንብረት የሆነውን “ኤ.ፈ.ር.ት” እንደ ቁም እንስሳት የመሳሰሉ የምርት ውጤቶች ወደ ሳውዲ መላክ ከጀመረ
ቆይቷል። ይህንን የንግድ ግኑኝነት እንዲጠነክር የሚያደርጉለት ደግሞ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ስም በሳውዲ የሚሰሩ የወያነ
ወኪሎች ናቸው። ስለዚ ወያኔዎች ሳውዲ የጥቅማቸው ምንጭ እንጂ ጎጂ አይደለም።
4) ሳውዲ ዓረቢያ በአፍሪቃ ቀንድ በተለይም በቀይ ባሕር ቀጠና ያላትን ጂኦ ፓለቲካዊ ንክክ የወያነ መንግስት ሊያሰጋው
የሚችል ነው። በተለይም ከዓባይ ግድብና ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ከግብፅ ጋር በመወገን ልታበጣብጥ ትችላለች በሚል
ስጋት እንቅልፍ ያሳጣቸው ጉዳይ ነው። በቅርቡ አንድ የሳውዲ ሚኒስትር ስለ ዓባይ ግድብ አሉታ ተናገረ ተብሎ የወያነ
መንግስት ምን ያህል እንደተርበደበደ ይታወሳል። ስለዚህ ወያነ ለግድቡና ለስልጣኑ ዕድሜ ማራዘም ሲል ሳውዲን በይፋ
ከማውገዝ ዝምታ ቢመርጥ የሚያስገርመን አይደለም።
5) ወያነ በዲያስፓራ ያለው የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ስለሚያስጋውና ለመቆጣጠርም ስለማይችል የትም ይሁን የትም
በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ጥቃት፣ መፈናቀልና ክብር መድፈር የሚያሳዝነው ሳይሆን የሚያስደስተው ነው። በሳውዲ
ዓረቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጠረው ችግርም አዛኝ መስሎ ለመታየት ቢሞክርም በአካባቢው ከሚገኙ የወያነ ወኪሎች ጋር
በመተባበር ለፓለቲካ ፍጆታ ሲባል እየተጠቀመበት ይገኛል። በተለይም የስርዓቱ ደጋፊ አይደሉም በሚባሉ ወገኖች
እንዲባረሩና ተገደው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ በማድረግ በስተጀርባ ብዙ ጉድ እየተሰራ መሆኑን የሚጠቁሙ ብዙ
መረጃዎች እየወጡ ናቸው። ስለዚ ወያነ በስደተኞች ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ሶቆቃ በሀገር ቤት ላሉ ወገኖቻችን “እኔን
ብትቃወሙ መውጫ መግቢያና መለመኛ ቦታም የላችሁም” በማለት ተስፋ ቆርጠው የስርዓቱን ባርነት ተቀብለው እንዲኖሩ
የሚጠቀምበት እንጂ ከህዝብ ጋር ለመወገን የሚያስችል ሞራል የለውም።
በማጠቃለል፡- ለራሱ ነፃ ያልወጣና በራሱንና በህዝቡን የማይተማመን የዉጭ አገልጋይ የሆነ የወያነ መንግስት ለዜጎች
ርህራሄና ጥብቅና በመቆም ከጥቃት ይከላከላል ወይም ያወግዛል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። በዓረቦች ጉርሻና ጡጦ ተወልዶ
ያደገውን የወያነ ቡድን ለህዝብና ለሀገር ክብር በቁርጠኝነት ይቆማል ብሎ ማሰብም የባሰ የዋህነት ነው።
ይባስ ብሎ ወያነ የሳውዲ ሰው በላ መንግስትን በማውገዝ ሳይሆን የተጠመደው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ነው የዘመተው።
ትናንት በኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገንድ ቁጣቸውና ተቃውሞቻቸው ለመግለፅ አደባባይ የወጡትን ንፁኃን ዜጎቻችን ፍቃድ
በመከልከል ብቻ ሳይሆን በማሰርና በመደብደብ እስር ቤት እያጎራቸው ይገኛል። ይህንን እርምጃ ለመውሰድ የተገደዱበት
ምክንያት ደግሞ ለሳውዲ ነገስታት ለማስደሰትና ታማኝነታቸውን ለመግለፅ ሲሆን በአንፃሩ የህዝባችን ሞራል እንዲደቆስና
አንገቱን እንዲደፋ ለማድረግ ነው። ከሳውዲ ተመለሱ የተባሉትም ከጥቂቶቹ በስተቀር ብዙዎቹ የት እንደገቡና ወዴት
እንደተወሰዱም የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ታዛቢዎች እየገለፁ ነው።

No comments:
Post a Comment